አዕምሯዊ የመማር ብልሐቶች የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት የማሻሻል ሚና፤ በሰባተኛ ክፍል ተተኳሪነት

Authors

DOI:

https://doi.org/10.59122/135108D

Abstract

የጥናቱ ዓላማ አዕምሯዊ የመማር ብልሃቶች የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት የማሳደግ ሚና መፈተሽ
ነው፡፡ ዓላማውን ለማሳካት በ2011 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ በጊዮርጊስ ትምህርት ቤት በመማር ላይ የሚገኙ የሰባተኛ ክፍል
የአማርኛ ኢአፍፈት ተማሪዎች ሦስት መማሪያ ክፍሎች በአመቺ ንሞና ተመርጠዋል፡፡ ተሳታፊዎቹ በብልሃት 42፣ በብልሃትአልባ 38
እና በቁጥጥር 38 በድምሩ 118 ሲሆኑ፣ በአንብቦ መረዳት ፈተናና በማንበብ ተነሳሽነት የፅሁፍ መጠይቆች አማካይነት መረጃ
ሰጥተዋል፡፡ የተሰበሰበው መረጃ በገላጭና በድምዳሜያዊ ስታትስቲክስ (በባለሁለት ተላውጦ ልይይትና በባዕድ ናሙና ቲ-ቴስት
ተሰልቶ) ተተንትኗል፡፡ የጥናቱ ውጤቶችም በብልሃትና በብልሃትአልባ አቀራረቦች የተማሩት በተለመደው የማንበብ ትምህርት
ከተማሩት ይልቅ በአንብቦ መረዳት ችሎታቸው ጉልህ መሻሻል አሳይተዋል፡፡ ነገርግን በማንበብ ተነሳሽነት ላይ ጉልህ ሚና አላሳዩም፡፡
በብልሃትና በብልሃት አልባው ቡድን መካከልም የአንብቦ መረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት ጉልህ ልዩነት እንደሌለ ተረጋግጧል፡፡
ይህም ከሁለቱ የብልሃት አቀራረቦች አዕምሯዊ ብልሃትን በይዘትነትና በትግበራ መማርና በትግበራ ብቻ መማር ልዩነት እንደሌለው
ያሳያል፡፡ ስለዚህ ትግበራው በሁለቱም ቡድኖች ስለሚገኝ በይዘትነት ከመማር ይልቅ በትግበራ መማር አስተዋፅኦ እንዳለው
ያመለክታል፡፡

443 95

Downloads

Download data is not yet available.

Author Biography

  • Hailay Tesfay Gebremariam, Arba Minch University

    Assistant Professor in Teaching Amharic (TeAm)

Downloads

Published

2020-12-01

Issue

Section

Full Research Article

How to Cite

አዕምሯዊ የመማር ብልሐቶች የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት የማሻሻል ሚና፤ በሰባተኛ ክፍል ተተኳሪነት. (2020). Ethiopian Journal of Business and Social Sciences, 3(2), 67-81. https://doi.org/10.59122/135108D

Most read articles by the same author(s)